በክልሉ ኪነ ጥበብ ለህዝቦች ትስስርና ለገዢ ትርክት ግንባታ ያለውን ትልቅ ሚና ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

ኪነ-ጥበብና ስነ-ጥበብ ለህዝቦች አብሮነትና ለገጽታ ግንባታ በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፓርት ቢሮ ለ2ኛ ጊዜ የተዘጋጀ ክልላዊ ውድድር በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ባስተላለፉት መልዕክት ኪነ ጥበብ የሰው ልጅ የሚኖርበትን ዘመንና ጊዜን መሠረት አድርጎ የአኗኗር ሁኔታን በስነጽሁፍ፣ ሙዚቃ ፣ ስነጥበብ ፣ ቲያትር፣ በሲነማ የሚገልጽበት ነጥበብ ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል ።

ኪነጥበብ የሰዎች ለሰዎች ትስስርን የሚያጠናክር እንደሆነም የተናገሩት የቢሮ ሃላፊ ዘርፉ ለዘላቂ ሰላምና አንድነትም ትልቅ ሚና እንዳለው አብራርተዋል።

ኪነ ጥበብን ለህብረብሔራዊነትና ለገዢ ትርክት ግንባታ መጠቀም እንደሚገባም አቶ ፋንታሁን አስረድተዋል።

የቢሮው ምክትል ሃላፊና የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ሃላፊ አቶ አክሊሉ ለማ በበኩላቸው ኪነጥበብና ስነጥበብ በማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊና ፓለቲዊ እንቅስቃሴ ላይ የሚጫወተው ሚና ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል ።

ይህ ውድድር ዋና ዓላማ አድርገው ያነገበው አዳዲስና ነባር የጥበብ ቤተሰብ ለመፍራትና ቀጣይ በሀገር ደረጃ ለሚካሄደው የኪነጥበብ ስነጥበብ ውድድር ብቁና ወሳኝ የጥበብ ቤተሰብ ለመመልመል እንደሆነም አስረድተዋል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ፀሐይ ደርጫ ቢሮው በመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የኪነጥበብና ስነጥበብ ውድድሩ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ስሆን የስዕል ፣ የውዝዋዜ ፣ የትወና፣ የቁኔጅናና ሌሎችም የጥበብ ስራዎች ለታዳሚዎች እንደሚቀርብ ታውቋል።

ውድድሩን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፤ የሐዋሳ ትምህርት ኮሌጅ መምህራንና እንዲሁም የጪዳ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ መምራን በዳኝነት ይመሩታል።

አጠቃላይ በክልሉ የሚገኙ ስድስቱም ዞኖች በውድድሩ የተሳተፉት ስሆን የስድቱም ዞን የባህል፣ ቱሪዝም ና ስፖርት መምሪያ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ሲል ደሬቴድ ዋካ ቅርንጫፍ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *