በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ለ6 ፖሊስ መኮንኖች የረዳት ኮሚሽነርነት የማዕረግ ዕድገት ተሰጣቸዉ።

Spread the love

የማዕረግ ዕድገት የተሰጣቸውም
1ኛ ረዳት ኮሚሽነር ከበደ ደበበ
2ኛ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ካሣ
3ኛ ረዳት ኮሚሽነር በዛብህ ገዝሙ
4ኛ ረዳት ኮሚሽነር ገበራ ገብሬ
5ኛ ረዳት ኮሚሽነር ኃይሌ ጪማ እና
6ኛ ረዳት ኮሚሽነር ኃብታሙ መላኩ ናቸው

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እና የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ ለ6 ረዳት ኮሚሽነሮች ማዕረግ አልብሰዋል።

ለበርካታ ዓመታት በፖሊስ ተቋም መስራታቸውንና በሠሩባቸው ውጤታማ ተግባር የማዕረግ ሽልማት በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።

ለሠራው አካል እውቅና መስጠት ለቀጣዩ ተግባር ይበልጥ የሚያነሳሳ ነው በማለት ለማዕረጉ ያልደረሱ አባላትንም ለውጤታማ ተግባር የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

ማዕረጉ በክልሉ በአደባባይ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ይህም የፖሊስ ግርማ ሞገስ ከፍ የሚያደርግ መሆኑም በመርሃ ግብሩ ተገልጿል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *