

የማዕረግ ዕድገት የተሰጣቸውም
1ኛ ረዳት ኮሚሽነር ከበደ ደበበ
2ኛ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ካሣ
3ኛ ረዳት ኮሚሽነር በዛብህ ገዝሙ
4ኛ ረዳት ኮሚሽነር ገበራ ገብሬ
5ኛ ረዳት ኮሚሽነር ኃይሌ ጪማ እና
6ኛ ረዳት ኮሚሽነር ኃብታሙ መላኩ ናቸው
የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እና የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ ለ6 ረዳት ኮሚሽነሮች ማዕረግ አልብሰዋል።
ለበርካታ ዓመታት በፖሊስ ተቋም መስራታቸውንና በሠሩባቸው ውጤታማ ተግባር የማዕረግ ሽልማት በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።
ለሠራው አካል እውቅና መስጠት ለቀጣዩ ተግባር ይበልጥ የሚያነሳሳ ነው በማለት ለማዕረጉ ያልደረሱ አባላትንም ለውጤታማ ተግባር የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።
ማዕረጉ በክልሉ በአደባባይ ሲሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ይህም የፖሊስ ግርማ ሞገስ ከፍ የሚያደርግ መሆኑም በመርሃ ግብሩ ተገልጿል።
በፍቅር ከበደ
