ምዘናው የመምህራንና የትምህርት አመራር እውቀትና ክህሎት ለማጎልበት እንደሚያስችል ተገለጸ ።

Spread the love

‎ክልላዊ የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና በይፋ ተጀምሯል።

‎ዛሬ በይፋ በተጀመረው ክልል አቀፍ ምዘና በሁሉም ደረጃዎች ከ7200 በላይ ነባር መምህራን ፣ርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀዉን የፅሑፍ ምዘና እንደሚወስዱ ታውቋል።

‎ምዘናውን በይፋ ያስጀመሩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የሙያ ብቃት ምዘናው የመምህራንና የትምህርት አመራር እውቀትና ክህሎት ለማጎልበት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

‎አቶ አልማው አክለውም በይፋ የተጀመረው የመምህራንና የትምህርት አመራር የሙያ ብቃት ምዘና በክልሉ በሁሉም አከባቢዎች በ12 የተለያዩ ማዕከላት እና ወደ 24 በሚጠጉ የምዘና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

‎የክልሉ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ አካሉ አለማዬሁ በበኩላቸው ምዘናው እያንዳንዱ መምህራንና የትምህርት አመራር በሙያቸው ውጤታማ እንዲሆኑ በማስቻል ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።

‎ምዘናውን በብቃት መወጣት ቀጣይ በሚኖረው የመምህራንና የትምህርት አመራር ጥቅማጥቅም ውጤታማነት ያለው ሚናም ከፍተኛ እንደሆነ ተብራርቷል።

‎የምዘናው የታርጫ ማዕከል አስተባባሪና የቢሮው የትምህርት ዕቅድ ዝግጅትና ሀብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አድማሱ ድብሎ በበኩላቸው ፈተናው ስኬታማ እንዲሆን ሁሉም የባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን በተገቢው እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

‎በመጨረሻም የቢሮው ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ ለሁሉም ተፈታኞች መልካም እድል እንዲሆን መመኘታቸዉን ‎ የቢሮው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *