



በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 56 ሺህ 56 ሺህ ላሞችና ጊደሮችን በሰው ሰራሽ ዘዴና በተሻሻሉ ኮርማዎች ማዳቀል መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ በበጀት አመቱ 56 ሺህ ላሞችና ጊደሮችን በሰው ሰራሽ ዘዴና በተሻሻሉ ኮርማዎች በማዳቀል 26 ሺህ 610 ጥጆች ማግኘት መቻሉን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።
አቶ ማስረሻ አክለውም ከአምናው ተመሳሳይ አመት በዝርያ ማሻሻል ከ23 ሺ በላይ ለሞችና ግደር በማዳቀል ከ14 ሺ በላይ ጥጆችን ማግኘት ተችሏል ብለዋል።
