በክልሉ 56 ሺህ ላሞችና ጊደሮችን በሰው ሰራሽ ዘዴና በተሻሻሉ ኮርማዎች ማዳቀል መቻሉ የክልሉ ግብርና ቢሮ ገለጸ ።

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 56 ሺህ 56 ሺህ ላሞችና ጊደሮችን በሰው ሰራሽ ዘዴና በተሻሻሉ ኮርማዎች ማዳቀል መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ ገልጿል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በክልሉ በበጀት አመቱ 56 ሺህ ላሞችና ጊደሮችን በሰው ሰራሽ ዘዴና በተሻሻሉ ኮርማዎች በማዳቀል 26 ሺህ 610 ጥጆች ማግኘት መቻሉን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።

አቶ ማስረሻ አክለውም ከአምናው ተመሳሳይ አመት በዝርያ ማሻሻል ከ23 ሺ በላይ ለሞችና ግደር በማዳቀል ከ14 ሺ በላይ ጥጆችን ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *