





ብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ከቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ጋር በመሆን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄደ ነው።
በዚህ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ ( ዶ/ር ) እንደተናገሩት የፓርቲውን፣ የመንግስት እና የአገራችን ስኬቶች ለአለም በማስተዋወቅ ውጤቶች ተመዝግበዋል።
በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋ እየተሻሻለ የመጣበት ነው ብለዋል።
የሰለጠነና ዘመናዊ የፖለቲካ ባህል እሳቤ እየጎለበተ የመጣበት ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጠው ውጤት ማሰመዝገብ መቻሉን ገልፀዋል።
ህብረ ብሄራዊት ትርክት እንዲጎለብት በማድረግ የሚዲያ ኮሚኒኬሽን ዘርፍ አበርክቷቸው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር)።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ቅንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ ገ/መስቀል ጫላ እንደገለፁት በድህረ እውነት ዘመን የሚነዙ አፍራሽ አስተሳሰቦችን ለመመከት ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ መጠቀም ይገባል።
የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ፓርቲው ያስመዘገባቸውን ስኬቶች ለህዝብ ማስተዋወቅ ይገባቸዋል ብለዋል።
