የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤቶች በመንግስትና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ የተጠናከረ ግንኙነት በመፍጠር የሚጫወቱት ሚና የላቀ መሆኑ

Spread the love

የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤቶች በመንግስትና በንግዱ ማህበረሰብ ዘንድ የተጠናከረ ግንኙነት በመፍጠር የሚጫወቱት ሚና የላቀ መሆኑን የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው ከክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤትና ባለ ድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አድርጓል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት በመንግስት እና በንግዱ ዘርፍ ያለውን ክፍተት በመቅረፍ በኢኮኖሚው ዕድገት ውስጥ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።

በዚህም የንግዱ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት በንግድ ስርዓት ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይቶ በመቅረፍ እና ችግሮችን በማጥበብ በመንግስት እና በንግዱ ዘርፍ ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖር አድርገዋል ብለዋል።

በሚዛን አማን ከተማ በተደረገው የምክክር መድረክ ሁለት የመወያያ ሰነደች በአቶ አምዴ ፋሪስና በአቶ አንተነህ አዲሱ ቀርቧል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የንግድና ኢንቨስትመንት ምክትል ቢሮ ኃላፊና የንግድ ሬጉላቶሪ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አምዴ ፋሪስ በንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት እና የመንግስት ጠንካራ ግንኙነት ለብልጽግና በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል ።

መንግስትና የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት በጋራ ተቀናጅተው በመስራት የግሉን ዘርፍ በማበረታታት ንግድና ኢንቨስትመንትን ማነቃቃት ይገባልም ብለዋል።

በዚህም ሂደት በጋራ በቅንጅት በመስራት ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድን መከላከል ይኖርብናል ሲሉም አብራርተዋል ።

የንግድ ስርዓትን በማዘመን ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ውድድርን በማስፋት በኩል የንግዱ ማህበረሰብ ትኩረት በማድረግ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አንተነህ አዲሱ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት አደረጃጀትን የተመለከተ ሰነድ አቅርበዋል።

አቶ አንተነህ አዲሱ ለባለድርሻ አካላት ባቀረቡት የመወያያ ሰነድ የክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ለንግዱ ማህበረሰብ የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠት ዓላማ አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል ።

የክልሉን ንግድና ኢንቨስትመንት የማሳደግ፣ በመንግስትና በንግዱ ህብረተሰብ መካከል እንደ አገናኝ ድልድይ ሆኖ ማገልገል የምክርቤቱ ዓላማው መሆኑንም ጠቅሰዋል ።

ምክርቤቱ የክልሉ ምርቶች እና አገልግሎቶች በዓለም አቀፍና በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁና ገበያ እንዲያገኙ ትኩረት አድርጎ ይሰራልም ብለዋል አቶ አንተነህ።

በቀረቡ የመወያያ ሰነዶች ላይ ከተሳታፊዎች አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በክልሉ ህጋዊ የንግድ ስርዓት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ስራዎችን በትብብር ለመቅረፍ በቅንጅት እንደሚሰሩም ተናግረዋል ።

መድረኩን ያጠቃለሉት አቶ ተመስገን ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ህገ_ወጥ ንግድን የመቀነስ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ቢሮው ከክልሉ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት

ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

በታጠቅ አበበ

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌በሊንክደን

https://www.linkedin.com/company/southwest-communications

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *