ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን በጋራ በተባባረ ክንድ በጽናት ተግዳሮቶችን በመቋቋም ጣፋጭ ድልና ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን በጋራ በተባባረ ክንድ በጽናት ተግዳሮቶችን በመቋቋም ጣፋጭ ድልና ስኬቶችን ማስመዝገብ ችሏል፦ ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

‎ኢትዮጵያውያን በጋራ በተባባረ ክንድ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በጽናት ተቋቁሞ ጣፋጭ ድልና ስኬቶችን መቀዳጀት ችሏል ስሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገልጿል።

በክልሉ እየተከበረ ያለዉን ‎የጳጉሜ 01 ቀን አስመልክቶ መልዕክት የክልል ርዕሰ መስተደድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እኛ ኢትዮጵያውያን በህብረ ብሔራዊ አንድነትና ትብብር ስንቆም የማንወጣው ዳገትና የማንሻገረው አንድም ፈተና የለም ብለዋል።

‎በዚህም በታላቁ በህዳሴ ግድብ ያየነውን ትብብርና የተቋቋምነው መሰናክል የፈጠርናቸው አንድነትና ያስገኘነው ጣፋጭ ድል ባለፉት መቶ አመታት ውስጥ ከገኘነው ድል የላቀ ታላቅ ድል እንደሆነ ገልጸዋል።

‎ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል እንደ ሀገር፣እንደ መንግስት በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁማ በድልና በፅናት እየተሻገረች ትገኛለች ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም ለዛሬው ጣፋጭ ድል አብቅቶናል ብለዋል።

‎ህብረ ብሔራዊ አንድነት ፣ወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴቶችን ይበልጥ በማጠናከር የሚገጥሙን ፈተናዎች ጊዜያዊ መሆናቸውን በውል በመገንዘብ እጅ ለእጅ ተያይዘን የጀመርነውን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ የበረታን ሆነን መገኘት አለብን ብለዋል።

‎የኢትዮጵያውያን የቁጭትና የላብ ውጤት የሆነው ህዳሴ ግድብ የፅናት ተምሳሌታችን መሆኑን አብራርተዋል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን 👇

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/

📌በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et

📌በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications

📌በትዊተር twitter.com/sweprs

📌በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi

📌በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab

📌በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication

📌በዋትስአፕ

https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x

📌https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *