




የሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ቲካሻ ቤንጊ በሸኮ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የብሔሩ ተወላጆችና ወዳጆች በተገኙበት በፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።
በፓናል ውይይት መድረኩ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ወ/ሮ ዘሙ ተስፋዬና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የ ቤንች ሸኮ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
