የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 46ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 46ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡

በዚህም መሠረት፦

1ኛ.የቀረቡ የኢንቨስትመንት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል። በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን በግብርና 27፣ በኢንዱስትሪ 4 እና በአገልግሎት 2 በአጠቃላይ 1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎችን መርምሮ ወደ ስራ እንዲገቡ ወስኗል።

2ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ የገቢ ግብር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ወደ ምክር ቤት መርቷል። እንዲሁም የታክስ አስተዳደር ደንብ መርምሮ አጽድቋል።

3ኛ. መስተዳድር ምክር ቤቱ የገጠር ኮሪደር ሥራዎች ዙሪያ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *