የብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ ለሸኮ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ እንኳን ለሸኮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ቲካሻ ቤንጊ” በሰላም አደረሳችሁ ብልዋል።

አቶ ጌታቸዉ በመልዕክታቸውም የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ “ቲካሻ ቤንጊ” ፈጣሪ ላደረገው ሁሉ ምስጋና እና የምርቃት ስነስርዓት የሚፈጸምበት በዓል መሆኑ ተናግሯል።

የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ “ቲካሻ ቤንጊ ” በአደባባይ የሚከበር የአብሮነትና ወንድማማችነት እንዲሁም እህትማማችነት ይበልጥ የሚጎላበት ትልቅ እሴት መሆኑ ገልጸዋል።

በዓሉ ለሰላምና ለአብሮነት ትልቅ ግምት የሚሰጥ፣ የባህል አንድነትና ትስስር የሚገለጥበት፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚጠናከርበት ካሉ ቱባ ባህሎች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

“ቲካሻ ቤንጊ ፣ ይበልጥ ለምቶ በአካባቢው ማህበረሰብ የኢኮኖሚያዊ፣የማህበራዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት እየጎለበተ እንዲመጣ ሚናው የጎላ መሆኑንም ዋና አፈጉባኤ በመልዕክታቸው አክሎበታል።

በድጋሚ እንኳን ለሸኮ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ቲካሻ ቤንጊ”በሰላም በጤና አደረሳችሁ ሲሉ የተከበሩ አቶ ጌታቸዉ መልካም ምኞታቸውን መመኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *