የክልሉን የመሠረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የአዳዲስ መንገዶችና ድልድዮች ግንባታና ጥገና ኘሮጀክቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ኘሮግራም የቴክኒክ ኮሚቴ ውይይት መድረክ ተካሄደ።

የውይይት መድረኩም በ2018 ዓም እስካካሁን የተከናወኑ ተግባራት እና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።

‎የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የገጠር መንገድ ትስስር ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ጌዲዮን እስጥፋኖስ ባደረጉት ንግግር፣የክልሉን የመሠረተ ልማት ፍላጎት ለማሟላት የአዳዲስ መንገዶችና ድልድዮች ግንባታና ጥገና ኘሮጄክቶች ላይ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ከ2017 ጀምሮ በ6 ወረዳዎች ላይ የመንገድ መሠረተ ልማት ኘሮጄክቶች ላይ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

በ2017 በጀት ዓመት የ6 መንገዶች ጥገና ኘሮጄክት ዕቅድ ተይዞ 4ቱን በማጠናቀቅ 2ቱን ወደ 2018 በጀት ዓመት በማሸጋገር በአሁን ጊዜ አንዱ ርክክብ ተደርጎ የተቀረው በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝም አክለዋል።

በ2018 በጀት ዓመት 14 የመንገድ ኘሮጄክቶች ግንባታ የሚሰራ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 7ቱ ከባለፈው በጀት ዓመት የተሸጋገረ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በቢሮው የገጠር ትስስር ለምግብ ዋስትና ኘሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ቀለመወርቅ የ6 ወራት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 ኘሮጀክቶች ዕቅድ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በ2018 በጀት ዓመት 11 የመንገድ ጥገና ኘሮጄክቶች እና 16 የአነስተኛ ድልድይ እንዲሁም የ7 ተንጠልጣይ ድልድይ ኘሮጄክቶች ግንባታ ስራ እንደሚከናወንም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በዚህም መሠረት በ2018 በጀት ዓመት 7 አዲስ መንገድ ግንባታ እና 10 አነስተኛ ድልድይ ኘሮጄክቶች የዲዛይንና ማማከር ስራዎች መጠናቀቃቸውን በመግለፅ የ4ቱ የድልድይ ዲዛይንና መማማር ስራ እንዲሁም የ6 የመንገድ ጥገና ኘሮጄክቶች ውል መገባቱን አስረድተዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የትራንስፖርት ዘርፍ ሃላፊ ኢንጂነር ዘመዴ አንዳርጌ የውይይት መድረኩን በመሩበት ወቅት እንዳስታወቁት፣አስካሁን ባለው ሂደት ያለውን ሀብት በማስተባበር በመንገድ መሰረተ ልማት ኘሮጄክቶች የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉንና አሁን በቀሪ ወራት በጊዜና በጥራት ማጠናቀቅ እንዲቻል ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በካሳሁን አሰፋ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *