የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በተገኙበት አስጀምሯ።

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፋት መልዕክት ይህ ስራ ለዜጎች መሰረታዊ አገልግሎት ለመስጠት ታልሞ የሚከናወነው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አካል መሆኑን ጠቁመው የሁሉንም ዘርፎች ምሉዕ አቅም ለማሳካት በዲጂታል ኢትዮጵያ መደገፍ አለባቸው ብለዋል።

ባለፉት ስድስት አመታት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ስርዓት መሸጋገሩን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ ብዛት እየጨመረ ባለበት ከተማችን ንቁ የዜጎች ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተው ዛሬ ወደስራ የገባው መተግበሪያ በapp ስቶር እና playstore የሚገኝ ሲሆን ዜጎች ወንጀልን ለመከላከል በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮ፣ በድምፅ፣ በሰነድ ወይም በቀጥታ በመደወል ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ሁሉም ዜጋ የአካባቢያችንን እና ከተሞቻችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *