


የደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኞች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ እወዳለሁ ብለዋል።
ፈጣሪ የሟች ወድሞችና እህቶችን ነፍስ በአፀደ ገነት እንዲያኖር ዘንድ ፀሎቴ ነው ብለው በአደጋው ሕይወታችን ላጡ ወገኖች ቤተሰብ ወዳጅ እና ዘመድ መፅናናትን ተመኝተዋል::
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጸጋዬ ማሞም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትናንት ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸዉን ላጡ ወገኖች ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማቸዉ በመግለጽ የወገኖቼ ነፍሳቸው በሠላም ትረፍ፣ለቤተሰቦች መጽናናትን ተመኘሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወንድም በሆነዉ ህዝባችን ይህ አደጋ በመድረሱ በጣም አዝኛለሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ በዚህ አደጋ ምክንያት ህይወታቸዉን ላጡ ወገኖች ፈጣሪ እረፍቱን እንድሰጣቸዉና ለቤተሰቦቻቸዉ መፅናናትን እመኛለሁ ስሉ መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
