በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በ73ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው።

Spread the love

በዛሬዉ ዕለት በቦትሰዋና ጋባሮኒ የተጀመረዉ 73 ኛው የአፍርካ አህጉር የአለም ጤና ድርጅት መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ይገኛል።

ይህ 73 ኛው የአፍሪካ አህጉር ከዓለም ጤና ድርጅት ስድስት የአህጉራዊ አስተዳደር አካላት አንዱ ሲሆን 47 አባል ሀገራት ያሉት የአፍሪካ ክልል ሀገራት የሚወክሉበት ኮሚቴ ነው፡፡

በመድረኩም ከ20 በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የጤና አጀንዳዎች ላይ ዉይይት የሚደረግ ሲሆን የ2023 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም እንዲሁም የአፍርካ ማህበረሰብ ጤና አሁናዊና ቀጣይ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ከአለማችን ማህበረሰብ ጤና ጋር ያለዉ አጠቃላይ ሁኔታ በመድረኩ ቀርበው ምክክርና ውይይት የሚደረግ ይሆናል።

በተጨማሪም 4 የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዙ ሰነዶች ቀርቦ በአባል አገራት እንደሚጸድቁ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ የተለያዩ መግለጫዎችን በመድረኩ የምታቀርብ ሲሆን በጎንዮሽ መድረክም ልዑካን ቡድኑ የሚሳተፍ ይሆናል።

መድረኩም ለቀጣይ 5 ቀናት በቦትሰዋና ጋባሮኒ የሚቀጥል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *