ምግብና ሥርዓተ-ምግብን በማሻሻል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።ADSCD

Spread the love

‎በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ከምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር ለእንስሳት እርባታ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና በቦንጋ ከተማ እየተሰጠ ነው።

‎በስልጠናው መድረክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በክልሉ ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታመነ በቀለ ባለፉት አራት አመታት በሌማት ትሩፋት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት የተሻለ መነቃቃት የታየባቸው ናቸው ብለዋል።

‎ቢሮው ምግብና ሥርዓተ-ምግብን በማሻሻል የቤተሰብ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል።

‎የሌማት ትሩፋት ሥራን ከተለመደው የእርባታ ዜደ የተሻለ በማድረግ በምርቶች ላይ እሴት በመጨመር የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማሳደግ ላይ ትኩረት መደረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎የእንስሳት ተዋጽኦ በኢትዮጵያዊያን ማዕድ ላይ የቅንጦት ምግብ መሆን የለበትም ያሉት አቶ ታመነ ያሉንን ሀብቶች ተጠቃሚ ለመሆን ጠንክሮ መስራት ይጠይቃል ብለዋል።

‎ኢትዮጵያ ከ70 ሚልየን በላይ የዳልጋ ከብቶች፣ 57 ሚሊየን ፍየሎችና 42 ሚሊየን ያህል በጎች ያሏት ሀገር መሆኗን ተናግረው ፤ እነዚህን ሀብቶች ምርታማነታቸውን በማሻሻል ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባሻገር መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

‎በክልሉ በእንስሳት እርባታው ዘርፍ ከ15 እስከ 20 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ጠቁመው ፤ በቀጣይ በስፋት መስራትና የማሳደግ ተግባር የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ ይሆናል ብለዋል።

‎በሌማት ትሩፋት ፓኬጅ ላይ የተዘጋጀውን የስልጠና ሰነድ በቢሮው የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይረክተር ወይዘሮ መሰለች ታደመ እያቀረቡት ይገኛል ሲል ቦንጋ ኤፍኤም ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *