በካፋ ዞን “የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ትጋት”በሚል መሪ ቃል ለዞን ማዕከል የመንግስት ሰራተኞች ሥልጠና እየተሰጠ ነው

Spread the love

በዚህ ወቅት ተገኝቶ የማስጀመሪያ መልዕክት ያስተላለፉት የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪና የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት ሀገራዊ ጥቅም ከሚያስገኙ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉም ዜጋ የጋራ አረዳድ ሊኖረው ይገባል አቶ ብለዋል።

የታደሠ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ቁመናና የመላው ኢትዮጵያዊያን ትጋት አስፈላጊነት ላይ ትኩረት ያደረገ ሥልጠና ለካፋ ዞን ማዕከልአጠቃላይ የመንግስት ሰራተኞች እየተሰጠ ነው።

የካፋ ዞን የብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ በመክፈቻ ንግግራቸው ሀገራዊ ጉዳዮችእና ብሔራዊ ጥቅሞች ዙሪያ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ የጋራ አቋም እንዲይዝ ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን አቶ ታከለ አንስተዋል።

በሀገራዊ የጋራ አጀንዳዎች ዙሪያ የብሔራዊ ጥቅሞችን ከማስከበር ረገድ ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ከዝምታ ይልቅ በያገባኛል ስሜት ልዩ ትኩረት ሊሰጥ ይገባልም ብለዋል::

የኢትዮጵያን ከፍታ የሚወስኑ ጉዳዮች ዋናው የጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና በመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ሀገርን ከማስቀደም አንጻር ሁሉም የጋራ ሀሳብ ላይ መድረስ ያስፈልጋል ብለዋል።

የሥልጠና መድረኩ በተለያዩ አዳራሾች ተከፋፍሎ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን ሰነዱ በተመደቡ የዞን አመራሮች ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት እየተደረገ ይገኛል::

በመድረኮቹ ለሀገር የሚጠቅሙ እና አሻጋሪ ጉዳዮች ተነስቶ በመወያየት በሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ዘንድ የጋራ ግንዛቤ ይያዛል ተብሎ ይጠበቃል ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *