“የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!!” በሚል መሪ ቃል ለታርጫ ማዕከል የመንግሥት ሰራተኞች ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።

Spread the love

“የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!!” በሚል መሪ ቃል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለታርጫ ማዕከል የመንግሥት ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠና መድረክ ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን ሚና በአግባቡ ሊወጣ እንደሚገባ ተብራርቷል።

ኢትዮጵያ ሉአላዊነቱንና ጂኦ_ስትራቴጂያዊ ተጠቃሚነቷን በማስጠበቅ፣ ለዜጎች ክብርና ለጋራ ተጠቃሚነት ቅድሚያ ሰጥታ ትሰራለች።

የብሔራዊ ጥቅማችንን እንዳናስከብር ከውጪና ከውስጥ ማነቆ የሚሆኑ ጉዳዮችን በተገቢው በመረዳትና በመለየት በጋራ መከላከል ይገባልም ተብሏል።

ስልጠናው በክልሉ በታርጫ ክላስተር የሚገኙ የክልል ተቋማት አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት በየተቋማት እየተሰጠ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

ስልጠናው በየተቋማት ሀላፊዎች በገለፃና በውይይት መልክ በመሰጠት ላይ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *