የጃንቹ ተራራና የሙዝ ደን

Spread the love

የወረዳው ሕዝብ የመንግስትን የልማት አቅጣጫ ተቀብሎ የመተግበር ልምድ ያዳበረ ለመሆኑ ማሳያ ነው።

የቤንች ሸኮ ዞን በሁሉም ወረዳዎቹ ተመሳሳይ ምርት የሚመረትበት ነው። ይህ የሙዝ ምርት የሚዛን አማን ከተማን ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎችም ይመረታል። የምርቱ መጨመር የአካባቢ የሙዝ ገበያን አረጋግቷል። ለአብነትም በሚዛን አማን ከተማ አራቱ በ20 ብር ሲሸጥ የነበረ የበሰለ ሙዝ አሁን በግማሽ ቀንሶ በ10 ብር እየተሸጠ ነው።

የዞኑ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃ፣ ደንና አየር ንብረት ለውጥ እና ኅብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ እንደሚሉት፤ በዞኑ ከአምስት ዓመት በፊት 29 ሺህ ሄክታር የነበረው የፍራፍሬ ማሳ ዛሬ 84 ሺህ ሄክታር ደርሷል፤ከዚህም ውስጥ 44 ሺህ ሄክታር ማሳን የሸፈነው ሙዝ ነው።

አሁን የተተከለው የሙዝ ችግኝ ሙሉ በሙሉ ምርት መስጠት ሲጀምር የምርት ማቅረብ አቅሙ ከፍ ይላል፤ ሙዙ በተፈጥሮ አፈር ላይ የሚበቅል እና የውጭ ንግድ ደረጃን የሚመጥን ተፈጥሯዊ ልዩ ጣዕም ያለው ምርት ነው።

በሌላ በኩል የሙዝ ምርቱ ረጅም ኪሎ ሜትር ሳይጓዝ በቅርበት እሴት ታክሎበት ለገበያ የሚቀርብበትን ዕድል ለመፍጠር በቀጣይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ርብርብ እንደሚደረግ ነው የሚናገሩት፤አምሯቹ አርሶ አደር ተገቢውን ዋጋ ከምርቱ አግኝቶ ተጠቃሚነቱን እንዲያሳድግ ‘የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ በአካባቢው ያስፈልጋል’ የሚል እምነት አላቸው።

ሙዝ ለቤንች ሸኮ እና አካባቢው ጥላ ነው፤ ምርቱ ምግብ ነው፤ ከምሽት ገበያ እስከ ማዕከላዊ ገበያ ተጭኖ በመሸጥ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ሀብት ነው፤ ስለዚህ በጅምር ሥራዎች የታየው ለውጥ አድጎ ከፍ እንዲል ለአርሶ አደሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር ተገቢ ነው።

የአንድ አካባቢ ልማትና ዕድገት የአካባቢ የተፈጥሮ ፀጋን መሠረት ያደርጋል፤ የተፈጥሮ ሀብቶችን በአግባቡ ለይቶ ተስማሚ የልማት ሥራዎችን ማስፋፋት ከተቻለ የሚፈልገውን ለውጥ የማያመጣበት ምክንያት አይኖርም፤ በሌላ በኩል ለአንድ ምርት የማይሆነውን አካባቢ “አይሆንም በቃ”ብሎ እጅ እግር አጣጥፎ ከመቀመጥ ይልቅ የሚሆነውን አጥንቶ መተካትን ከጃንቹ አርሶ አደሮች የተራራው ሙዝ ልማት መማር ይቻላል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *