የህዝብን ተጠቃሚነት ሊያሳድግ የሚችሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ገለጹ

Spread the love

በዳውሮ ዞን በ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት እና የፓርቲ ክንፍ የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ተገምግሟል።

የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳር አቶ ዳዊት ገበየሁ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የህዝብን ተጠቃሚነት ሊያሳድግ በሚችል መልኩ መንግስትና ፓርቲ በመቀናጀት እየሠሩ ይገኛል።

በሁሉም የልማት ዘርፎች አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲቻል ወጥ የሆነ የአመራር ቁመና እና ቁርጠኝነት ያስፈልጋልም ብለዋል።

የመንግሥትን የትኩረት አቅጣጫ በመከተል የማህበረሰብን የኑሮ ሁኔታ ለማረጋጋት በሚያስችሉ ጉዳዮች እና በአመራሩ ልዩ ትኩረት የሚመሩ ተግባራትን በቅንጅት መምራት እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

የዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መላኩ ተረፈ በበኩላቸው በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲው መሪነት ሰፊ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙም ገልፀዋል።

በውጤት የታጀበ ተግባር ለማየት እና ሁለተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በየ ደረጃው የሚገኙ አመራሮች የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እና 5 ሚሊዮን ኮደርስ ጨምሮ ሌሎች ፓርቲው ያወረዳቸውን ኢንሸቲቮች ለማሳካት አመራሮች ኃላፊነታቸውን በትጋት እንዲወጡ አቶ መላኩ አሳስበዋል።

በዳውሮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም አላንቦ የእስካሁኑ አፈፃፀም ጥሩ ጅምር ቢኖረውም በቀሪ ወራት ተግባራትን ቆጥረው በመረከብና በማስረከብ ይበል የሚያሰኝ ሥራ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በመድረኩ የየወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም አቅርቦ ተገምግሟል ።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የማህበረሰብን የልማት እና የመሠረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ እንዲቻል ከላይኛው መዋቅር ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ፓርቲውን በተቋማት መትከል ይጠበቅብናል ያሉት አሰተያየት ሰጪዎች የፓርቱውን ኢኒሼቲቮች እንዲሁም መንግሥት ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች በመከተል ሁለተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

በተነሱ ሀሳቦች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር በቀጣይ ተግባራት ላይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ መድረኩ መጠናቀቁን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *