ቢስት ባር ለአለም ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ

Spread the love

የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ቢስት ባር ለአለም ለማስተዋወቅ የቅስቀሳ ስራው በተገቢው መከናወኑን የዞኑ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አስታወቀ።

በአሉ በድምቀት ለማክበር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን በቤንች ሸኮ ዞን የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በአል ቢስት ባር ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ ጥር 4 እና 5/2018 በታላቅ ድምቀት በቤንች ሸኮ ዞን በሸይቤንች ወረዳ በዣዥ ቀበሌ እና በሚዛን አማን ከተማ በአማን አየር ሜዳ ላይ ይከበራል ።

በአሉ የተጣላ የሚታረቅበት፣ የደረሰ እህል የሚቀመስበት፣ በይቅርታ እና ምህረት የሚታለፍበት በአል በመሆኑ በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ይሰጠዋል።

የበአሉ መከበር የህዝቡን የእርስ በእርስ ትስስራቸውን ይበልጥ የሚዳብርበትና ባህላቸው ወደፊት የሚወጣበት መሆኑን የሚዛን አማን ከተማነዋሪዎች ተናግረዋል።

በአሉ የብሔረሰቡ ተወላጅ በአል ብቻ አይደለም ያሉት ነዋሪዎቹ፥ ከሌሎች በዞኑ ከሚኖሩ ብሔረሰቦች ጋር በጋራ በአሉን በድምቀት ለማክበር መዘጋጀታቸውንም ጠቁመዋል።

የሚመጡ እንግዶችን በተገቢው በመቀበል በአሉ በሰላም ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮምንኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላቸው ጎንደር በበኩላቸው በአሉ የአደባባይ በአል እንደመሆኑ የብሔረሰቡ ባህል ለማስተዋወቅ በሚዲያ ለማጀብ የቅስቀሳ ተግባራት በተገቢው መከናወን መቻሉን ጠቁመዋል ።

በአሉ የቤንች ብሔረሰብ ብቻ አይደለም ያሉት አቶ በላቸው በዞኑ የሚገኙ ህዝቦች በጋራ የሚያከብሩት በመሆኑ ለየት እንደሚያደርገውም ጠቁመዋል።

ወጣቶችም በአላቸውን አውቀው ከማስቀጠል አንጻር ብዙ እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል ሲል ደሬቴድ ሚዛን ቅርንጫፍ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *