የክልሉ ኦዲት ግብረ ኃይል በቤንች ሸኮ ዞን የክዋኔና የአካባቢ ኦዲት አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ገመገመ

Spread the love

‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ዋና ኦዲተር አቶ አስራት አበበ የክልሉ ምክር ቤት የተለያዩ የኦዲት ውጤቶችን በጋራ ከገመገመ በኃላ በክዋኔ ኦዲት የተሰሩ ስራዎች በተጨባጭ ታች ተወርዶ መታየት እንዳለባቸው ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል ።

‎መድረኩ በዋናነት የኦዲት ግኝት በአግባቡ ስለመመለሱ ማረጋገጥ እና በዚህ ላይ በአግባብ ያልፈጸሙ አካላትን ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ይሆናል ብለዋል።

‎ከዚህ በፊት በስፋት ያልተሄደበት ዘርፍ በመሆኑ የክልሉ ኦዲት ግኝት ግብረ ኃይል በዚህ ልክ ወርደው መደገፋቸው አስፈላጊ እንደሆነ ዋና ኦዲቴሩ ገልጸዋል ።

‎ግብር ኃይሉ በቤንች ሸኮ ዞን ከ2014 እስከ 2016 ዓ.ም የስራ ዕድል ፈጠራ ሥራ፣የኢንቨስትመንት ስራዎች የተደረገው የክዋኔ ኦዲት ማስተካከያ ያለበትን ደረጃ እየገመገመ መሆኑን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *