




በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት ክልላዊ ማጠቃለያ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በመርህ ግቡሩ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች በሰልፉ ለመታደም የመጡ ልዑካን ቡድኖች ትርዒት እያሳዩ ይገኛል።
ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ እና በኅብረት እያዘሙ ደስታቸውን በአደባባይ በመግለጽ ላይም ይገኛሉ።
ከመፈክሮችም ውስጥ:-
በህብረት ችለናል፣
ግድቡ የእኔ ነው፤
የአብሮነታችን ምሰሶ!
የህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት፣
የህዳሴ ግድብ ! የብልጽግናችን አሻራ፣
ግድባችን፣ አገር ወዳድነታችንን ከቃል በላይ፣
ህዳሴ የወል እውነታችን የሚሉ እና ሌሎችም ይገኙበታል።
በዕድገቱ በዛብህ
