




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን በማስመልከት ህዝባዊ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በኅብረት ችለናል’ በሚል መሪ ሐሳብ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ከክልሉ ከሁሉም ዞኖች ከተለያዩ አደረጃጀቶች የተወጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የደስታ ስሜታቸውን በተለያዩ መልዕክቶች በመግለፅ ላይ ናቸዉ።
በድጋፍ ሰልፉ መረሐ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ንና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በፍቅር ከበደ
