የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቁን በማስመልከት ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ ክልላዊ ማጠቃለያ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ሰልፉ ”በህብረት ችለናል” በሚል መሪ ሃሳብ የክልሉ የአስተዳደር እና ፖለቲካ ማዕከል በሆነችው ቦንጋ ከተማ እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በስልፉም የክልሉ ነዋሪዎች የተሰማቸውን ደስታ በአደባባይ እየገለጹ ይገኛሉ ።

እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ከክልሉ በተለያየ ማህበራዊ መሠረት የመጡ ሰልፈኞቹ የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ መልዕክተቶችን እያሰሙ ይገኛሉ።

ከመፈክሮቹ መካከል ”ሕዳሴ ግድብ በደም የከበረ በላብ የታረሰ” ፣ ”ህዳሴ ግድብ የብልጽግና አሻራ፣ ”ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችንና የአብሮነታችን ምሶሶ”፣ህዳሴ ግድብ የደም፣የላብ ፣የእንባና የውሃ ጠብታ ድምር ውጤት፣”ሕዳሴ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ፣ህዳሴ የወል እውነታችን፣ሕዳሴ የሁለተኛው የአርበኝነት ድላችን የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች ይገኙበታል።

በክልላዊ ማጠቃላያ ሰልፉ ስነስርዓት የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ዋና አደባባይ የሚካሄድ ይሆናል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *