

በዛሬው ዕለት ፍትህ ሚኒስቴር ባዘጋጀው አህጉር አቀፍ ባህላዊ ግጭት አፈታት ኮንፍረንስ ላይ በሀገር ደረጃ ከተመረጡ አራት ክልሎች አንዱ በመሆን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልን በመወከል የካፋ ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት (Qaabbitino) ተመርጧል።
በዚህም በካፋ ዞን ሺሾእንዴ ከተማ ከቀጠና 1-4 የተመረጡ የባህላዊ ፍርድ ቤት ዳኞች( ሽማግሌዎች) አለመግባባቶችን እንዴት በባህላዊ መንገድ እንደሚፈቱ ለታዳሚዎች አሳይቷል ሲል
የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
