
በሸካ ዞን 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
“ሀገራዊ መግባባት ለህብረ-ብሔራዊ አንድነት”በሚል መሪ ቃል በዞኑ ባሉ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር ቆይቶ ዞናዊ ማጠቃለያው በቴፒ ከተማ ተካሂዷል።
የሸካ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዮሀንስ ካሳሁን እንደገለፁት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ “ሀገራዊ መግባባት ለህብረ -ብሔራዊ አንድነት ” በሚል መሪ ቃል ብዝሃነትን በማስተናገድ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች መብት መከበር ዋስትና የሆነው የኢፌዲሪ ህገ መንግስት የፀደቀበት በህዳር 29 ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ኩነቶች እየተከበረ መቆየቱን ተናግረዋል።
ዋና አፈጉባኤ አክለው ሀገራዊ መግባባትን የሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ የመፍትሔ ሀሳብ በማፍለቅ የሕዝቦችን አብሮነትና ትስስር በማጠናከር ሀገራዊ ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባም ተናግረዋል።
በዞኑ ከቀበሌ ጀምሮ በተለያዩ ኩነቶች የፌደራልዝምና ህገ መንግስት አስተምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሊሆን በሚችል መልኩ በየደረጃው እየተከበረ የመጣው በዞን እና በክልል ደረጃ ተከብሮ በአርባምንጭ ከተማ የሚጠቃለል መሆኑን ዋና አፈጉባኤው ገልፀዋል።
የበዓሉ መከበር ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ህብረ ብሄራዊ ነታቸውን የሚያጠናክር ፣ ባህላቸውን እንዲያስተዋውቁ እኩል ዕድል መፍጠር መቻል ፣ በቀጣይ ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ስርዓት መጎልበት በጋራ ጠንክሮ እንዲሰራ መሆኑን ዋና አፈጉባኤው ተናግረዋል ።
ኢትዮጵያዊያን የሚኖሩ የጋራ ጥያቄዎችን በህገመንግስቱ መሰረት እያቀረቡ ለህገ መንግስቱ ተገዥ በመሆን አንድ የሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ በተለይ ማተኮር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
ለፓናል ውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ በህብረ -ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ግንባታ ዙሪያ የሸካ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳንኤል አድራሮ ያቀረቡ ሲሆን ብዝሃነት በማስተናገድ ፤ ህብረብሔራዊ ፌደራሊዝም በመገንባት የፌደራሊዝምን ስርዓትን አጠናክሮ መሄድ በርካታ ችግሮችን ይቀርፋል ብለዋል።
አቶ ዳንኤል አክለው በህገ መንግስቱ ላይ ያሉ አተገባበሮች በሚገባ በማየት የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ መቅረፍ ይገባል ብለዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በዓሉ መከበር የብሔር ብሐረሰቦች እንድተዋወቁ ህብረ ብሐራዊ አንድነት እንዲጠናከርና እንድጎለብት እንደሚያግዝ ጠቁመው ከምን በላይ ሀገራዊ መግባባት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሠራ እንደሚገባ መናገራቸውን የሸካ ዞን ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
በዓሉ ህብረ ብሔራዊነት እና ሀገራዊ አንድነት በሚጎለብትበት ከሸካ ዞን ወረዳና ከተማ አስተዳደር ከተወጣጡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማርዎች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድርና በተለያዩ ኩነቶች ሲከበር የዞን ፣ የከተማና የወረዳ አመራሮችና ሰራተኞች ፣የሀይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ጨምሮ የሸካ ዞን ፖሊስ አባላት የበዓሉ ታዳሚ ሆነዋል።
