የብልጽግና ፓርቲ የፎቶ አውደ ርዕይ በሳይንስ ሙዝዬም ተከፈተ

Spread the love

የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓልን አስመልክቶ የፎቶ አውደ ርዕይ በሳይንስ ሙዝዬም ተከፍቷል፡፡

በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ተመስገን ጥሩነህ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የፌደሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ አገኘው ተሻገር እና ሌሎች የፓርቲውና የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

እስከ ነገ ለዕይታ ክፍት በሚሆነው አውደ ርዕዩ÷ ፓርቲው ከምስረታው ጀምሮ አሁን የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳዩ ምስሎች ለእይታ መብቃታቸውን የፓርቲው መረጃ አመላክቷል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የሃሳብ ልእልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ መሆኑ ይታወቃል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *