




“ሀገራዊ መግባባት፤ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የዳውሮ ዞን ማጠቃለያ መርሃ-ግብር በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።
በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዳዉሮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዳዊት ሚኖታ፤ 19ኛው የኢትዮጵያ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዞኑ በተለያዩ ኩነቶች ከቀበሌ እስከ ትምህርት ቤቶች ደረጃ ሲከበር መቆየቱን ገልጸዋል።
ቀኑ የሚከበርበት ዋና ምክንያትም በሕዳር 29/1987 ዓ.ም የኢፌዲሪ ህገ መንግስት የጸደቀበት ቀን ሲሆን፤ ይህ ደግሞ በሀገራችን ታሪክ ብዝኃነታችንን በማስተናገድ ኢትዮጵያን የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ህግ መንግስታዊ ዋስትና ያገኘንበትን ቀን ለመስታወስ ይዘክራል ብልዋል።
ለብሔር ብሔረሰቦች እኩል መብት በህገ መንግስቱ የተሰጣቸውን ሲጠቀሙ እና እራሳቸውን በራሳቸው ሲያስተዳድሩ የጋራ ማንነት ጉዳይ፣ ፍትሃዊነትን፣ አካታችነትን፣ አሳታፊነትን ሁሉንም ባማከለ መልክ ለሁሉም እኩልነት የተረጋገጠበት ቀን መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ም/ቤት በጀት፣ ፋይናንስና ኦዲት ጉዳይ ቋሚ ኮምቴ ሰብሳብ ወ/ሮ የኋላሽት በላይነህ ተናግረዋል።
የወል ትርክትን መሰረት በማድረግ ታላቅ፣ ጠንካራ፣ የበለጸገች እና ዘላቂ ሰላሟን ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ገንብቶ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም አመላክተዋል።
በመድረኩ ሰነድ በቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀረበው ሰነድ መነሻ ከመድረኩ ጥያቄ ተንስቶ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል ሲል ደሬቴድ ዋካ ቅርንጫፍ ዘግቧል።
