የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ጥራት አጋዥ የሆኑ ኮምፒውተሮችን ለዞኖች አሰራጨ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ አትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ከካማራ ኢዱኬሽን ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ግዢ የተፈጸመባቸው ለትምህርት ጥራት አጋዥ የሆኑ ኮምፒውተሮችን ለዞኖች አሰራጭቷል ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምትክልና የስርአት ትምህርት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አባተ ኡቃ እንደገለጹት

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኮምፒውተር ግዢው እንደተፈጸ ገልጸዋል።

የኮምፒውተር ስርጭቱ የትምህርትን ስራ ከቴክኖሎጂ ጋር ለማገናኘትና ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ፕሮግራም መሆኑንም አቶ አባተ ገልጸዋል ።

በኮምፒውተሩ አዲሱ የትምህርት ፖሊሲ ፣ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት መጽሐፍት፣ የብዙ ጊዜ ኢንተራንስ ፈተናዎች ከነመልሶቻቸው፣ የኦንላይን ፈተናን ተማሪዎች እንዴት እንደሚሞክሩ፣ የተፈጥሮ ሣይንስ ኬሚካል ላብራቶሪ ሂደቶች እና ኢ-ለርኒንግ እንዲሁም የሌሎች ትምህርት አጋዥ መጽሐፎች የታጫነባቸው ኮምፒዩተሮች መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

259 ኮምፒውተሮች ከዞኖች በተሰበሰበ 3.3 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ ግዥ የተፈጸሙና የሸካ፣ቤንች ሸኮና ካፋ ዞኖች በዚሁ መሳተፋቸውን አቶ አባተ ኡቃ ተናግረዋል ።

ዞኖች ወረዳዎችን በማስተባበር ለትምህርት ጥራት መጠበቅ አጋዥ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በቅናሽ በመግዛት ተሳትፎ እንዲያደርጉም አቶ አባተ ጥሪ አድርገዋል ።

የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታደሰ በበኩላቸው ኮምፒተሩን በተረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ኮምፒውተሮቹ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል ።

በካፋ ዞን ለዚሁ ተግባር ከ600 ሺህ ብር በላይ ከዋቻ ከተማ አስተዳደር የተገኘ ሀብት ግዥ ላይ እንዲውል ተደርጓልም ብለዋል አቶ ተፈሪ ።

የተረከቡትን ኮምፒውተሮች በዋቻ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚሰራጭም አቶ ተፈሪ ተናግረዋል ።

በቀጣይም ይህንን ተግባር በዞኑ በሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ለማድረግ ከወረዳና ከተማ አስተዳደር የትምህርት መዋቅሮች ጋር አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉም አቶ ተፈሪ ተናግረዋል ።

በታጠቅ አበበ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *