



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ የ2017 የአንደኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ እንደገለጹት የፓርቲ አደረጃጀቶችን ተቋማዊ አቅም በማጠናከር የብልጽግና ህልሞችን ለማሳካት ከወትሮ በተለየ መልኩ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በየደረጃው ያለው የፓርቲው አደረጃጀቶች በፓርቲ እና በመንግስት የተቀመጡ የልማት ግቦችን ለማሳለጥ አይተኬ ሚና ማበርከት መቻሉን ጠቁመዋል።
የብልጽግና እሳቤዎች፣ህገ ደንቦች እና ትልሞችን ማሳካት የሚያስችል በአመለካከቱ የጠራ አባላት የማፍራት ቁልፍ ተግባር በመሆኑ ሁሉም በየደረጃው ያለው አመራር በትኩረት መስራት እንዳለበት ገልጸዋል ።
ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር ለፓርቲው የጀርባ አጥንት መሆኑን የገለጹት አቶ በላይ በህዋስና በመሰረታዊ ድርጅት የታዩት መልካም ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
በተግባር አፈጻጸም የታዩት ጥንካራ ጎኖችን በማላቅ ክፍተቶችን በፍጥነት በማረም ለህዝቡ የተገባውን ቃል እውን ለማድረግ በትጋት ማገልገል እንደሚገባ አስገንዘበዋል ።
በመድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ተሰማ ፣ የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አመራሮች፣ የዞን፣ የወረዳ ና የከተማ አስተዳድር የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።
