



የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራር አባላት የባህር ዳር ከተማን የልማት እንቅስቃሴዎችን እየተመለከቱ ነው።
በጉብኝቱ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር)፣የብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ መለስ አለሙ፣የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውና ሌሎች አመራር አባላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
አመራሮቹ በአሁኑ ወቅት በጣና ዳርቻ እየተገነባ የሚገኘውን ጣና ማሪና ፕሮጀክት፣ በከተማው የኮሪደርና ሌሎችንም የልማት እንቅስቃሴዎችን እየተመለከቱ ነው።
ልማቱ ከተማዋን ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹና ሳቢ የሚያደርጉ እንደሆኑም ተገልጿል።
የአመራር አባላቱ ከሰዓት በኋላ የብልፅግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
