በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የታርጫ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት በመሆኑ መደሰታቸውን የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

Spread the love

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች በበኩላቸው መናኸሪያው ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ንብረት ውጭ በሚያድርበት ወቅት ካለው ስጋት ነፃ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።

የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች አቶ ወ/ማርያም ብትሬ እና ወ/ሮ አባይነሽ ሳና ቀደም ሲል የታርጫ ከተማ መናኸራያ የመንገደኞች ማረፍያ፣ ካፍቴሪያ፣ የትኬት መቁረጫ ቢሮና መኪና ማቆሚያ ቦታ ምቹ ያለመሆኑን አንስተው አሁን ግን ዘመናዊ መናኸሪያ ተገንቢቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

በግንባታ ምክንያት ከመናኻሪያ የትራንስፖርት አገልግሎት ከአንድ ዓመት በላይ በመቋረጡ ከተወሰነው ታርፍ በላይ ለመክፈል መገደዳቸውን ነዋሪዎቹ አስታውሰዋል።

የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ተገቢ ቁጥጥር ስለሚደረግ ትርፍ ከመጫን እና ከታርፍ በላይ ከመክፈል እንደምታደጋቸው አቶ ወ/ማርያም ብትሬ እና ወ/ሮ አባይነሽ ሳና ገልጸዋል።

ሌላው የከተማ ነዋሪ አቶ ኡቴ ወ/ማርያም በትራንስፖርት ዘርፍ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ መንግስት ተገቢ ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርግ እንድሁም ህብረተሰቡ ህገ ወጥ ተግባር የሚፈጽሙትን በመጠቆም መተባበር ይገባል ብለዋል።

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች አቶ ወንድማገኝ ዶጌ እና አቶ ጌታቸው ተሾመ መናኸሪያ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ንብረት ውጭ በሚያድርበት ወቅት ካለው ከስርቆት ስጋት ነፃ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።

ባለንብረቶቹ ደንብና ስነ ሥርዓት ተከትለው ለህዝብ አግልግሎት እንደምሰጡም ተናግረዋል።

የታርጫ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ አበበ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ከህዝብ የወጡና ለህብረተሰብ አግልግሎት የሚሰጡ በመሆናቸው ተገቢ አግልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *