






በምረቃ ስነስርዓት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የለውጡ መንግስት በርካታ የተወዛዘፉ የቤት ስራዎችን ተቀብሎ ሲሰራ መቆየቱን አንስተው ዛሬ የተመረቀው የታርጫ ህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
የመነኸሪያ ያለመኖር ለዜጎች ለስምርት ምቹነት፤ የተሸከርካሪ ብቃት ለማረጋገጥ ፣ ተሳፋሪውን ተገቢውን ታርፍ ለማስከፈል ማነቆ ከመሆኑም ባሻገር ህዝብን ለእንግልት እያዳረገ መቆየቱን ተናግረው፤ አሁን የግንባታው መጠናቀቅ ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት እንደሚያግዝ አብራርተዋል።
በዘርፉ ከነዳጅ ስርጭትና ተሳፋሪውን ህዝብን በህገ ወጥ መንገድ በሚያማርሩ ህገወጥ አካላት ላይ መንግስት እንደማይታገስ ገልጸው፤ በተያያዘው የዋጋ ንረትን በሚያባብሱት ላይ ከህዝብ ጋር በመሆን ለመፍታት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ በአጽንኦት ተናግረዋል።
አክለውም የህዝብን ጥያቄ ለመመለስና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ተቋርጠው የቆዩ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅና አዳዲሶቹንም የልማት ስራዎችን ጀምረው ለህዝብ ክፍት ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ምርጫ የተለያዩ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሀሳባቸውን በማቅረብ የሚወዳደርበት መሆኑን አንስተው፤ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የምርጫ ሂደቱን ለማወክ በሚሰሩ አካላት ላይ ህዝቡ እንዲተባበር ጠይቀዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኢኮኖሚና መሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ ፕሮጀክቱ ብዙ ዓመታትን ያስቆጠረና በብዙ ባለድርሻ አካላት ርብርብ በመጨረሻ ክልሉ በተሰጠው ትኩረት በራስ አገዝ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ብልጽግና ተጀምሮ የተቋረጡ መሠረተ ልማቶችንና አዳዲስን ጀምሮ ማጠናቀቅ ባህል መሆኑን በማንሳት የክልሉን የመንገዶች ባለስልጣንን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቁ በቀጣይ አመስግነዋል።
የተመረቀው መነኸሪያ ለህዝቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ በትብብር መስራት እንደሚገባ አቶ ፋጂዮ አሳስበዋ።
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ይህ መነሃሪያ በክልሉ አማካኝነት በዞኑ ውስጥ እየተከናወኑ ካሉ በርካታ የመሠረተ ልማት ስራዎች አንዱ መሆኑን አንስተው፤ መጠናቀቁ የንግድና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሻግር መሆኑን ተናግረዋል።
የመነሃሪያው ግንባታ መጠናቀቅ ለብዙ ወጣቶች የስራ ዕድል ከመፍጠርም ባሻገር ለነጋዴዎች የንግድ ስርዓቱን እንደሚያቀላጥ አንስተው፤ ለስራው ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ሁሉ ምስጋና አቀርበዋል።
የታርጫ ከተማ ከንቲባ አቶ አስናቀ አበበ በመደመር ኢሳቤ በተሰሩ ስራዎች ብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፍ ውጤት መመዝገቡን አንስተው፤ ለዚህም የተረሳውን የሀላላ ካብ የዓለም ዓቀፍ የቱርዝም መዳረሻ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም በተሰጠው ትኩረት በከተማውም ትኩረት የተሰሩ ሰው ተኮር ተግባራት ለውጥ እያመጡ መሆኑን አንስተዋል።
ከ99 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባውን ዘመናዊው የታርጫ ከተማ መናኸሪያ ከ300 በላይ ተሽከርካሪዎችን በደረጃ የማስተናገድ አቅም በላይ በርካታ አገልግሎትን አካትተዋል።
በጌታሁን ግርማ
