


በከተማ አስተዳደሩ የሚዲያ አካላት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ከመትከል ባሻገር የተተከሉትንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ሀገር አቀፍና ክልላዊ የሚዲያ ተቋማት በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል ።
የሚዲያ አካላት በከተማ አስተዳደሩ ጋቡቃ መንደር በመገኘት ችግኝ የመትከልና በጽድቀት ላይ የሚገኙትን ምልከታ አድርገዋል።
በምልከታው ወቅት ከ2014_2016 ዓ/ም ድረስ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው መከናወናቸውን የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምስራቅ አስናቀ ለሚዲያዎች ተናግረዋል ።
በዚህም በተከናወነ የአካባቢና ውሃ ጥበቃ ስራዎች የተተከሉ ችግኞች 90 በመቶ መጽደቃቸውን አቶ ምስራቅ ተናግረዋል ።
ተተክለው በጸደቁ የግራቪሊያ ዛፍ የቁንዶ በርበሬ በስሩ በመትከል ከዘርፉ አርሶአደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ምስራቅ ለሚዲያዎች ተናግረዋል ።
በዚህም ተተክሎ በጸደቀው ማሳ 4 ሄክታር መሬት መሸፈኑንም አቶ ምስራቅ ገለጻ አድርገዋል።
ይህንንም መሠረት በማድረግ በከተማ አስተዳደሩ ጋቡቃ መንደር ገላጣና በድንጋይ ማዕድን ተቆፍረው ክፍት በሆኑ ስፍራዎች የሚዲያ አመራሮችና ጋዜጠኞች በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።
በታጠቅ አበበ
