




ኮሚሽኑ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ እውን እንዲሆን ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ 2017 ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና 2018 ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ በክልሉ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ እውን እንዲሆን እየተደረገ ያለውን ዘረፈ ብዙ በተቀናጀ ጥረቶች ውስጥ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።
በዚህም ለፓርቲ ጥንካሬ ውጤታማነት ፣ የውስጠ ፓርቲ ጤንነት ማስጠበቅ፤ የፓርቲ የፖለቲካ ጥራትና የሥነ- ምግባር ጤናማነት እንዲረጋገጥ አባሉና አመራሩ በፓርቲው ራዕይ፣ እሳቤዎች ህልሞችን ማዕቀፍ እንዲመራ በርካታ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በተግባር አፈጻጸም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማጎልበት ፣ተግዳሮቶችን ከወዲሁ በማረም ጠንካራ ኢንስፔክሽኝ በመፍጠር ጠንካራ ፓርቲና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ኮሚሽኑ ተልዕኮውን በቁርጠኝነት እንዲወጣ ብርቱ ትግል ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን እና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ሰብሳቢ ወ/ሮ ራሄል ሌዊ ኮሚሽኑ በመተዳደሪያው ደንብ መሠረት ፓርቲው ጠንክሮ እንዲወጣ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።
የፓርቲ የአሰራር ሥርዓት በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲከበር ማድረግ፣ የጸረ-ሙስና ትግል ተቋማዊ በሆነ መልኩና በየደረጃው አጀንዳ እንዲሆን ማድረግ፣የፓርቲ ሀብቶች ገንዘብ፣ ንብረትና ሰነዶች ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በአግባቡ እንዲጠበቅ ለማድረግ ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል።
በቀጣይ ለጠንካራ ኢንስፔክሽን ጠንካራ ኮሚሽን መርህን በመከተል ጠንካራ ፓርቲ ግንባታን ለማፋጠን በየደረጃው የሚገኝ የኦሚሽኑ አመራር ያለሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል።
በመድኩ የክልሉ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ አባላት፣የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳድር የኮሚሽኑ አመራሮች መገኘታቸዉን የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
