
👉 የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት ከፍተኛ ጫና ከተፈጠረባቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የመንግስት ሰራተኛው በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፡፡ በዚህ ምክንያት የጤና ባለሙያዎች፣መምህራንና በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ማሻሻያ እንዲደረግ ጥያቄ እያነሱ ይገኛሉ፡፡ የመንግስት ሰራተኛን የኑሮን ደራጃን ከማሻሻል አኳያ በመንግስት ምላሽ ዙሪያ ምላሽ ቢሰጥበት?
👉 መንግስት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንዳለ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ከቤት ፈላጊው ቁጥር ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ ገና ብዙ ስራ ይጠይቃል። መንግሰት በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ በከተሞች የታየውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ምን እየተሰራ ይገኛል?
👉 ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ እቅድ አፈጻጸም ከቁልፍ የኢኮኖሚ እድገት አመላካቾች አንጻር በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማብራያ ቢሰጥ?
👉 መንግስት ካለፉት ጊዜት በአንጻራዊነት የተሻለ ሰላም እያመጣን ነው ይላል ማሳያዎቹ ምንድናቸው?
👉 ጽንፈኞችን ከማህበረሰቡ ለመለጠል፣ የህዝቡን ሰላም ለማስጠበቅ፣ አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለመገንባት እንደሀገር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?
👉 ኢትዮጵያን ማተራመስና ህዝቡን ማወክ ሥራችን ነው ብለው የሚንቀሳቀሱ በአገር ውስጥና ውጪ አገራት የሚገኙ ጽንፈኞችን አደብ ለማስያዝ ከእያንዳንዱ ዜጋ ምን ይጠበቃል?
👉 በታችኛው የወረዳ መዋቅር ወረዳ፣ በዞን፣ በከተማ አስተዳደርና እስከ ክልል ድረስ ሙስናና ብልሹ አሰራር ህዝቡን በማማረር ላይ ይገኛል። ሙስና የሰላማችንና የልማታችን ጠንቅ የማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች፣ የተገኙ ውጤቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ቢሰጥ?
👉 ሀገራዊ የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ስኬታማ እንዲሆን የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጥ?
👉 አጠቃላይ የኮሪደር ልማት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ላይና በአፈጻጸም ሂደት ያለአግባብ ጥፋት እንዳይፈጸም በተለይም ክልሎች አካባቢ ጥንቃቄ ከማድረግ አኳያ ማብራሪያ ቢሰጥ?
