
ፍትሃዊ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ የዘመናት የባህር በር ጥያቄ በሰላማዊ፣ ህጋዊና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ የተጀመረው ሂደት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
ጎረቤቶቻችንና አፍሪካዊያን ወንድሞቻችን የባሕር በር ጥያቄውን ፍትሃዊነት እንዲረዱትና እንዲያግዙን፣ ወዳጅ ሀገራት ዓለም አቀፍ ተቋማት ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ምን እየተሰራ ነው?
መንግስት ደሀ ተኮር ሪፎርም አራማጅ ነኝ እያለ የመንግስት ሰራተኛውንና ዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል ሥራ የሚጀምረው መቼ ነው? ከከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ለመውጣ ምን ታስቧል?
መንግስት ተደጋጋሚ የንጹሃን የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ከሞት ድብደባና እንግልት ለመታደግ አግባብ ያለው የጸጥታ ኃይል የማይመድበው ለምንድነው?
መንግስት ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ያለው የጸጥታ ችግር በድርድር እንዲፈታ፣ የፖለቲካ እስረኞች መቼ ነው የሚፈቱት? ቶሎ ፍትህ ያለማግነት ችግር መቼ ነው የሚቀረፈው? ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ምን የሚሉት ነገር አለ?
በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ከ1998 ዓም ጀምሮ መኖሪያ ቤት ሰርተው ያለምንም ምትክ ቤት እና የገንዘብ ካሳ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎች ለምን በአግባቡ አይስተናገዱም?
ባለፉት ዓመታት በመንገድ፣ በመብራት፣ በመጠጥ ውሃ፣ ኢነርጂ እና መስኖ ዘርፍ ሀብት ተመድቦ ሲሰራ ቀይቷል፡፡ ነገር ግን ካለው የመሰረት ልማት ፍላጎት አኳያ ሲታይ ጉድለት አለ። ተጀምረው ያልተጠናቀቁና የተጓተቱ የመንገድ፣ የመስኖና የውሃ ግንባታዎችን በፍጥነት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲውሉ የተያዘው አቅጣጫ ምንድነው?
