ለዐይን ሕክምና ተቋማት አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል

Spread the love

መንግስት የዐይን ሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ገለጹ።

ሚኒስትር ዴኤታው በኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስፈጻሚ ካትሊን ኦቨርቤይ ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ዶክተር ደረጀ ኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የዐይን ህክምና ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ከሚሰሩ ድርጅቶች አንዱ መሆኑን ገልጸው የተቋሙ የሃኪሞች ስልጠና ለዘርፉ ከፍተኛ ጠቀሜታ እያስገኘ ነው ብለዋል።

ድርጅቱ በተለያዩ አካባቢዎች ለዜጎች የዐይን ህክምና አገልግሎቱት ተደራሽ በማድረግ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀዋል።

የጤና ሚኒስቴር ድርጅቱን ጨምሮ በዐይን ህክምና ላይ ለሚሰሩ ተቋማት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የኪዩር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ ካትሊን ኦቨርቤይ፤ ድርጅቱ በኢትዮጵያ እየተሰጠ የሚገኘውን የዐይን ህክምና ጥራት እና ተደራሽነት ለማሳደግ ለሃኪሞች ስልጠና መስጠቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በተለይም በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማት የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሳደግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር መስራት እንደሚፈልግ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *