


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብዝሃ ከተማ በሆነችዉ ቴፒ ከተማ ለሚገኙ የክልል ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አስመልክቶ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል።
ስልጠናዉ በዋናነት ሀገሪቲ ያላት ስትራቴጂካዊ ብሔራዊ ጥቅሞች ምንድናቸዉ ፣ ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ያሉ ዕድሎችና ፈተናዎች ምን ድናቸዉ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
የሀገራችን ሲቪል ሰርቫንቱና እያንዳንዱ ዜጋ መወጣት ስላለበት ኃላፊነትና ከተለያዩ ሀገራት ጋር ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ሀገሪቱ ስለምትከተለዉ አሰራር ጭምርም ያካተተ ነዉ።
ስልጠናዉን የቴፒ ማዕከል ቢሮ ኃላፊዎች በየቢሮዉ እየሰጡ ይገኛሉ ሲል ማሻ ኤፍኤም ዘግቧል።
