አመራሩ የግብርና ዘርፉን በተለየ ሁኔታ በመምራት ከዘርፉ የሚመነጨውን ሀብት ማግኘት ወሳኝ ጉዳይ ይሆናል፦ ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ግብርና ቢሮ የ2017 የምርት ዘመን የበጋ መስኖ ስንዴ እና መደበኛ መስኖ ዕቅድ ዙሪያ ከዞን ከወረዳና ከባለድሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል ።

በንቅናቄ መድረክ ላይ መድረኩ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የወተት ምርትን ለማሻሻል በእንስሳት ዝሪያ ማሻሻል ላይ በትኩረት መሠራት እንደሚገባ አንስተዋል ።

በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተጀመሩ ስራዎችን ከወትሮው በተለየ በተደራጀ ሁኔታ በማልማት ወደ ውጤት መቀየርና ወደ ሁሉም አከባቢ ማስፋት እንደሚያስፈልግ አክሏል ።

ለእንሰት ልማት ትኩረት በመስጠት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና በቡና ልማት ላይ በማተኮር የገቢ ምንጬን ለማሳደግ በቡና ዘር ብዜት ላይ ከወዲሁ በትኩረት መሠራት አለበት ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ ።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ

አቶ ማስረሻ በላቸው የበጋ ስንዴ ልማትም ሆነ የሌማት ትሩፋት ተግባራትን ለማሳካት የመንግስት ተቋማትና የባድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እንዳለው አሳስበዋል ።

በመደበኛ ስንዴ ልማትም 150 ሄ/ር በክላስተር ለማልማት ቢሮው የዘር ድጋፍ እንደሚያቀርብ አንስተዋል ።

ለተሳታፊዎች የ2017 ምርት ዘመን የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት እና መደበኛ የመስኖ ዕቅድ እንዲሁም የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ የ2017 ምርት ዘመን የመደበኛና የሌማት ትሩፋት ተግባራት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።

በ2017 ዓ/ም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት12,187 ሄ/ር በማልማት ምርታማነትን 41.2 ኩ/ል በማድረስ 502,667 ኩ/ል ምርት ለማግኘት መታቀዱ ተነስቷል።

በምርት ዘመኑ በመደበኛ መስኖ 83, 003 ሄ/ር በማልማት 18,743,728 ኩ/ል ምርት ለማግኘት መታቀዱ ተገልጿል ።

በሌማት ትሩፋት ላይም በምርት ዘመኑ 4 ሚለየን ዶሮ ቀብና ኮክኔ እንደሚሰራጭ ተገልጿል ።

በእንሰት ልማት ላይ 2,400,000 በ67 ችግኝ ጣቢያውን በማቋቋም እንደሚፈላ፤ 2,039,300 የእንሰት አምቾ ቀበራ እንደሚደረግ ተጠቅሷል ።

በውይይቱ ላይ በሁሉም ዘርፍ ያሉት አፈፃፀም እየተሻሻለ መምጣት፣ በዞኖች የግብርና ዘርፍን ለመደገፍ በጀት መመደቡ፣ በስንዴ ልማትና በአትክልትና ፍራፍሬ የማሳ ሽፋንም ሆነ ምርታማነት እያደገ መምጣቱ፣ተጨማሪ የመስኖ አውታሮች ተመርቀው ወደ ስራ መግባት በጥንካሬ ተነስቷል ።

በሌላ በኩል በምርታማነቱ በተፈለገው ልክ ያለመሆን፣ በእንስሳትና ዓሣ ልማት ዘርፍ የጥራት ጉድለት መኖሩ፣ የመኖ አቅርቦት ውስንነት፣ በእንስሳት ዝሪያ ለማሻሻል የናይትሮጅን እጥረት መኖር፣ የዶሮና እንቁላል ምርት በሚፈለገው ልክ ያለመሆን፣ ምርጥ ተሞክሮ ያለመስፋት በቀጣይ ትኩረት እንደምሹ ተገልጿል ።

በማጠቃለያው በጥንካሬ የተነሱት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባና በጉድለት የተነሱት ጉዳዮች ትኩረት በመስጠት በቅንጅት መሠራት እንዳለበት በማንሳት መድረኩ ተጠናቋል ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *