ለቃል መታመን ፕሮጀክቶችን ከውድቀት የመታደግ፣ የሀገርን ክብር የመመለስ እና የትውልድን ተስፋ የማደስ አዲሱ የኢትዮጵያ መንገድ
ለሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች እውነተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለጊዜያዊ የፖለቲካ ማክሸፊያ እና ለይስሙላ ፕሮፓጋንዳ ብቻ መሠረት ድንጋይ ተቀምጦላቸው የተተዉ፣ በሐሰተኛ ሪፖርት እና በብልሹ አሠራር የተተበተቡ በርካታ ፕሮጀክቶች ለአያሌ ዓመታት የኢትዮጵያውያንን የልማት ጥማት ሳያረኩ ቆይተዋል። ተፈጥሮ ሳይሰስትባት እና ጸጋ ሳይጎድላት “ነገን ሳይሆን ዛሬን ብቻ” በሚሉ አፍራሽ ዕሳቤዎች ወደ ኋላ ስትጎተት የኖረችው ሀገራችን፣ ለአላስፈላጊ የፋይናንስ ዕዳ እና ለከፍተኛ…
