በሸካ ዞን በቤተሰብ ዕቅድ ላይ የሚተገበር የፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

Spread the love

“የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ወደ ሁሉን አቀፍ ተደራሽነት ያለ ልዩነት ” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ሸካ ዞን በተመረጡ የጤና ተቋማት በጊዳቦ የፖሊስ አድቮኬሲ ሴንተር ድጋፍ የሚተገበር የ18 ወራት የቤተሰብ እቅድ የፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሸካ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ እምሩ ወየሳ የረጅም ጊዜ የቤተሰብ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የእናቶችን ጊዜ በመቆጠብና ወደ ጤና ተቋማት ምልልስን በመቀነስ የእናቶች ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር የቤተሰብ ምጣነን ለማስተካከልና ያልተፈለገ ዕርግዝና ለመከላከል ጠቃሚ መሆኑን አንስተዋል ።

የክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶችና ህፃናት ጤናና ስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶረት ዳይሬክተር አቶ መሠረት ወ/ማሪያም ፕሮጀክቱ በዞኑ በተመረጡ የጤና ተቋማት የጤና አገልግሎት አሰጣጥን በማሳደግ የእናቶችና ህፃናት ጤናን ለማሻሻል የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ወሳኝ በመሆኑ አገልግሎቱ ዝቅተኛ በሆነባቸው አካባቢዎች ለማገዝ የመጣውን ፕሮጀክት በመሆኑ በአግባቡ ወደ ስራ በማስገባት ለለውጥ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል ።

በመሆኑም የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል የጤና ባለሙያዎች በየተቋሞቻቸው በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የመድረኩ ዓላማ ፕሮጀከቱን ለሚተገበርባቸው ዞንና ወረዳዎች ለማስረከብ ያለመ እንደሆ ያነሱት በጤና ሚንስቴር የእናቶችና ህፃናት አፍላ ወጣቶች መሪ ስራ አስፈጻሚ የስነ ተዋልዶ ጤና፣ የቤተሰብ ዕቅድ፣ አፍላ ወጣቶችና ወጣቶች ጤና ዴስክ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰኚ ዱፌራ ናቸው።

ተልዕኮውም በክልሉ በሸካ ዞን በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎቱን በማሳደግ በተገቢው መንገድ ለእናቶች ለማሳለጥና ለማሰደግ እንደሆነ ተናግረዋል ።

የፕሮጀክቱ ያለፉት ዓመታት ልምድ፣ ውጤትና ያጋጠሙ ተግደሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የሚሰሩ ተግባራት ዕቅድና ዝርዝር የአፈፃፀም አቅጣጫ ለተሳታፊዎች በፕሮጀክቱ አስተባባዎች በአቶ ተስፋ ደምለውና በወ/ሮ ማርታ አሰፋ ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል ።

ራዕይውም በመረጃ ላይ የተመሠረተ የቤተሰብ ዕቅድ አገልገሎት ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 49 ያሉትን እናቶችን ተጠቃሚ በማድረግ የእናቶችን ጤና ለማሻሻል የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን የዕቅዱ አቅራቢ የሆኑት ወ/ሮ ማርታ አሰፋ አብራርተዋል ።

የፕሮጀክቱ ዓላማ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ለማሻሻል ምቹ ሁኔታን በማመቻቸት ስልጠና በመስጠት፣ የጤና ተመሠረተ ልማት በማሟላት፣ አስፈላጊ ግብዓቶችን በማቅረብ፣ ለስራ ምቹ አካባቢን በመፍጠር እንዲሁም የባህል ተጽዕኖዎችን በማስተማር ለማሻሻል ያለመ እንደሆነ ተነስቷል ።

ፕሮጀክቱ የሚያቅፋቸው በዞኑ ውስጥ በሚገኙ 39 ጤና ኬላዎችና 11 ጤና ጣቢያዎች 100% የአገልግሎት አሰጣጥን ግብዓት በማሟላት፣ ስልጠና በመስጠትና በተጠቃሚው ህብረተሰብ ዘንድ ግንዛቤውን በማሳደግ በማሻሻል የእናቶችን ተጠቃሚነትና እርካታ ለመጨመር እንደሆነ ተነስቷል።

በውይይቱ ወቅት ሁሉም የባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት በቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ዙሪያ የነበሩ ማነቆዎችን በጋራ በቅንጅትና በትብብር በመፍታት በዘርፉ ውጤታማነትን በማረጋገጥ የእናቶችን ጤና በማሻሻል እርካታውን ለማሳደግ በትኩረት መሠራት እንደሚገባ ተነስቷል ።

በፕሮጀክቱ አተገባበር ዙሪያ ግልፀኝነት በሚሹ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረኩ እና ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽ ተሰጥቷል ።

በመደረኩ ላይ የክልሉ ፋይናንስ ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ ሚለዮን አለሙን ጨምረው የክልሉ ጤና ቢሮ ከፍተኛ ባለሙያዎች፣ ከሸካ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊና ፕሮጀክት ከሚያቅፍበት ወረዳና ከተማ አስተዳደር የመጡ ባለሙያዎችና ሌሎች የባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *