ምቹ የእናቶች ማቆያ በማዘጋጀትና ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት በመስጠት የእናቶችና ህፃናት ሞት መቅረፍ ይገባል፦ አቶ ኃይለ ዘውዴaxda

Spread the love

‎የክልሉ ጤና ቢሮ እናቶች፤ ህፃናት አፍላ ወጣቶች ጤና እና ስነ-ምግብ ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም እና የ2018 ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

‎በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀይሌ ዘውዴ ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ የጤና ተቋማትን ለማስፋፋት በሰጠው ትኩረት አዳዲስ ጤና ተቋማት ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎በክልሉ 138 ጤና ተቋማትና 817 ጤናኬላዎች ከ የጤና አገልግሎት እየሰጡ ቢሆንም ከአገልግሎት ጥራት አንፃር የሚታዩ ውስንነቶች ሊቀረፉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

‎አቶ ኃይለ አክለውም ምቹ የእናቶች ማቆያ በማዘጋጀትና ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት በመስጠት የእናቶችና ህፃናት ሞት መቅረፍ እንሚመገባ ገልዋወል።

‎በእናቶች ምርመራና ወሊድ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ

‎በ2017 የተደራጀ ስራ መከናወኑን የጠቆሙት አቶ ኃይለ የወጣቶችና አፍላ ወጣቶች የቤተሰብ ዕቅድ ዙሪያ የታዩ ክፍተቶች መሻሻል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

‎የህፃናት ክትባት፤ የእናቶች ማቆያ ግንባታ፤ የአፍላ ወጣቶች ቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎትና የድህረ ወሊድ አገልግሎት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ኃላፊው ተናግረዋል።

‎በዳይሬክቶሬቱ የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞችን በማጠናር ውስንነቶችን ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባም ኃላፊው ገልጸዋል።

‎የክልል ጤና ቢሮ እናቶች፤ ህፃናት አፍላ ወጣቶች ጤና እና ስነ-ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሠረት ወ/ማሪያም በበኩላቸው በክልሉ ምስረታ ወዲህ በዘርፉ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።

‎ውይይቱ በተግባራት አፈፃፀም ወቅት የሚታዩ ክፍተቶች ለማሻሻል ግብዓት የሚሰበሰብበትና ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚረዳ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

‎በመድረኩ የዞኖችና በየደረጃው ያሉ ጤና ተቋማት የ2017 ዓ.ምና የ2018 ሩብ ዓመት አፈፃፀም ቀርቦ የሚገመገም ይሆናል።

‎በውይይቱ የክልሉ ጤና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፤ የዞን፤ የወረዳ እና በየደረጃው ያሉ ተቋም ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ ሲል ደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *