



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ “የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶችን ያማከለ ንቅናቄ ለነገው ትውልድ ግንባታ ሚና አለው ” በሚል መሪ ሀሳብ ለባለ ድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ: ሀገራችን ለጀመረችበት የማንሰራራት ጉዞ የሴቶችና ወጣቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
ወጣቶች ለሀገር ግንባታና ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ስርዓት መሪ ተዋናይ መሆናቸውን የጠቆሙት ኃላፊዋ: በፊታችን የሚካኸደውን ምርጫ ሠላማዊ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ከወድሁ አደረጃጀታቸውን በማጠናከር እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ህፃናትና ወጣቶች የነገው ትውልድ እንደመሆናቸው መንግስት የሚያወጣቸውን ፖሊሲ ሀሳቦች በመደገፍ ለራሳቸው የሚትመች ሀገር እንዲገነቡ አስገንዝበዋል።
ወጣቱ ክፍል የጥፋት ሀይሎች ተሳታፊ መሆን የለበትም ያሉት ወ/ሮ ገነት: በየመዋቅሩ ያሉትን የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶች በማፅናት በስነ ምግባር የታነፁ እና ምክንያታዊ ማህበረሰብ እንዲገነቡ ጥሪ አቅርበዋል።
አሁን ያለንበት የዲጂታል ዘመን ለጥቅምና ለጥፋት የሚውልበት እድል ስላለ ወጣቶች ነቅተው ለወላጆችና ለሀገር ብልፅግና በሚውልበት አኳኃን እና በኃላፊነት እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።
በመድረኩ የክልሉ ባለድርሻ አካላትና አመራሮች፣ የተለያዩ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀቶች፣ የማህበራት እና ፌደሬሽኖች ተወካዮች እየተሳተፉበት ነው።
በአሻግሬ ገ/ወልድ
