





የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የ2017 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የአስፈጻሚ ተቋማት ዕቅድ አፈጻጸም በቦንጋ ከተማ እየገመገመ ነው።
የህግ፤ ፍትህና መልካም አስተዳደር ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ፤ማህበራዊ ጉዳዮች ዘርፍ ፤ግብርና እና ገጠር ልማት፤ከተማና መሠረተ ልማት ዘርፍ ፤እንዲሁም በጀት፤ ፋይናንስና ኦዲት ጉዳዮች ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴዎች ናቸው አፈጻጸሙን እየገመገሙ የሚገኙት።
የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ጸሀይ ዳርጫ በወቅቱ እንደገለጹት የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት በሁሉም ዘርፍ እንዲረጋገጥ የህዝብ ውክል ስራዎችን አስፈፃሚ ተቋማት የህዝብ ውክልና ስራዎችን በተገቢው እንዲወጡ አሳሰቡ።
የህዝቡ ተጠቃሚነት በተግባር እንዲረጋገጥም ስራዎችን በየጊዜው መከታተልና መገምገም ያስፈልጋልም ብለዋል።
ግምገማው በአስፈጻሚ ተቋማት በ1ኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን ቋሚ ኮሚቴዎች በጥልቀት በመገምገም የጋራ መግባባትን ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ እንደሆነም አፈ ጉባኤዋ ገልጸዋል።
በዚህም አስፈጻሚ ተቋማት የህዝብን ውክልና በተግቢው እንዲወጡና የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችም የጀመሩትን የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እንዲያጠናክሩ አስገንዝበዋል።
ቋሚ ኮሚቴዎች በቡድን ሆነው የየዘርፍ የተቋማት አፈጻጸም በመግምገም ላይ ናቸው።
በፍቅር ከበደ
