
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ የበዓሉን አከባበር ቅደመ ዝግጅት ስራዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ መቱ አኩ እንደገለፁት 19ኛው በሀገር አቀፍ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ የብሔረሰቦች ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ሀገራዊ መሪ ቃሉ ላይ በቂ ግንዛቤ በመያዝ በዚህም መነሻ ከክልሉ ምክር ቤት ጋር የጋራ ዕቅድ በማዘጋጀትና ክልላዊ የበዓሉ አብይ ኮሚቴ በማዋቀር ወደ ስራ የተገባና እያንዳንዱ ዞን የራሱን ዕቅድ ወስዶ ተግባራትን በማውረድ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የተከበሩ አቶ መቱ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ክልላችን ደረጃ የበዓሉ ኩነት ከታች ከቀበሌ ጀምሮ ያለውን ማህበረሰብ ወጣቶችን፣ ሴቶችንና የትምህርት ተቋማትን እንዲሁም መላውን ማህበረሰብ ባሳተፈ መልኩ እንዲከናወን ታስቦ አሁን በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች እየተጠናቀቀ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ምክር ቤቱ ክልሉን ተጨማሪ አቅም ልሆኑ የፌዴራልዝምና ህገመንግሥት አስተምህሮ ላይ አሰልጣኞች ስልጠና ከወሰዱ አካላት፣ ከዞን ምክር ቤት አፈጉባኤዎችና ከሚዲያ አካላት ጋር በዓሉ እንዲደምቅና መግባባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መሠረት በማድረግ ውይይት የተደረገበት አግባብ መኖሩን አቶ መቱ ገልፀዋል።
በበዓሉ የብሔረሰቦች የጋራ ዕሴቶች ደምቀው እንዲታዩ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ዋና አፈ ጉባኤው የተከበሩ አቶ መቱ አኩ አብራርተዋል።
በአሁኑ ሰዓ በዓሉ በክልሉ ከቀበሌ ጀምሮ በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አከባቢዎች በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ቦታዎች መላው ህብረተሰብ ባሳተፈ መልኩ በድምቀት በመከናወን እየተጠቃለለ እንደሚገኝ ጠቅሰው በህዳር 22 ቀን በክልል ደረጀ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማሳተፍ የሚጠቃለል እንደሚሆንም አቶ መቱ አስረድተዋል።
ይህ በዓል ሲከበር በሰፊው ለሀገር፣ ለህዝብና ለትውልድ የሚጠቅም ነገሮች ላይ መሠረት በማድረግ በጋራ አብሮ መቀጠል የሚያስችሉ ሂደቶችን የሚናስቀጥልበት በዓል መሆኑን እንደለበትም ዋና አፈ ጉባኤው ጠቅሰዋል።
በክልሉ ውስጥ ያለው ብዝሃነት ተምሳሌት በሀገር ደረጀ ከፍ ብሎ እንዲታይ ክልላዊ የቅድመ ዝቅጅት ሂደቱም ይህንን ታሳቢ በሚያሳይ መልኩ እየተከናወኑ መሆናቸው አቶ መቱ ገልጸዋል።
አቶ መቱ አኩ አክለውም በክልሉ ውስጥ ያሉ 13 ብሔረሰቦች መልካም ልማዶች፣ ቱባ ባህሎችና የጋራ እሴቶች አቅም ለሀገር ጥሩ የሆነ መነሻ ስንቅ እንደሚሆኑም አንስተዋል።
የዘንድሮው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ የብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአርባምንጭ ከተማ “ሀገራዊ መግባባት ለህብራ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል የሚከበረ መሆኑን የጠቆሙት ዋና አፈጉባኤ በዚህም የክልሉ ባህል ልዑካን ቡድን የክልሉን ህዝብ መልካም ባህል፣ ማንናትና እሴቶችን በማሳየት በዓሉ የደመቀ እንዲሆን ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
