የገቢ ግብርን ከማሰባሰብ ባሻገር በዘርፉ የሚታየውን ህገ ወጥ አሠራርና ማጭበርበርን በመግታት የህግ ተጠያቂነት ማስፈን በቀጣይ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ተገለጸ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ገቢዎች ቢሮ በግብር ህግ ማስከበር ዘርፍ የግብር ህግ ማስከበር ዳይረክቶሬት ለታክስ መረጃ አደራጅ፣ ለታክስ ህግ ተገዥነትና የስጋት ስራ አመራር ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል ።

የቢሮ ምክትል ኃላፊና የግብር ህግ ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በላይ በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የዘርፉ ባለሙያዎች ለዘርፉ ስራ ልዩ ትኩረት በመስጠት በግብር አሰባሰብ ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመቀነስ መሥራት እንደሚገባ በአጽንኦት አንስተዋል።

አክለውም ገቢውን ከማሰባሰብ ባሻገር በዘርፉ የሚታየውን ህገ ወጥ አሠራርና ማጭበርበርን በመግታት የህግ ተጠያቂነት ለማስፈን የኦፍሬሽን ስራ ማጠናከር በቀጣይ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ አስገንዝበዋል ።

ለውጤታማነቱ ዞኖች ለታችኛው መዋቅር የሚሰጡ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ማጠናከር፣ ከላይኛው ተቋምና የባለድርሻ አካላት ጋር መናበብ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ሰነዱን ለሰልጣኞች ያቀረቡት አቶ ጎበዜ ጎበና የታክስ ስጋት ስራ አመራርና ኦድት ዳይረክቶሬት ዳይሬክተሩ ስልጠናው በዘርፉ የሚታየውን የግንዛቤ ክፍትን በመቅረፍ የኦድት ስራውን እንደሚያቀላጥፍ አነስተዋል።

ግብር ከፋዩን ከስህተት በመጠበቅ ወደ ህግ ተገዥነት እንደሚያመጣ፣ የተጠያቂነት ስርዓትን እንደሚዘረጋ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ድጋፍና መናበብን እንደሚያጠናከር አቶ ጎበዜ ገልጸዋል።

አስተያየት ሰጪዎቹ ስልጠናው አሳታፊ መሆኑን በመግለጽ በዘርፉ በአድስነት የተቀላቀሉ ባለሙያዎች ዘንድ የነበረውን የክህሎት ክፍተትና ብዥታዎችን በመቅረፍ ወቅታዊ መረጃ በማሰባሰብ፣ የህግ ተገዥነትን በማስፈን፣ የገቢ አቅምን ለማሳደግ እንደሚረዳ አንስተዋል ።

ስልጠናው ባለሙያዎች በቂ ግንዛቤ በመጨበጥ በግብር አዋጆችና ደንቦች ላይ ግብር ከፋዩን በማስተማር ግብር ከፋዩን ከተጠያቂነት ለማዳንና በዘርፉ የሚከሰቱ ማነቆዎችን በመፍታት የገቢ ግብርን አሟጥጦ ለማሰባሰብ እንደሚያግዝ ገልጸዋል ።

ከወቅታዊ መረጃ አሰባሰብ፣ ከኦድትና ስጋት ስራ አመራር አካባቢ የሚታዩ ችግሮችን በመፍታት ዘርፉን በማዘመን በየደረጃው የታቀደውን የገቢ ዕቅድ በተገቢው በማሰባሰብ የክልሉ ዕድገት እውን ለማድረግ እንደሚያግዝ በመግለጽ ለተግባራዊነቱ ቅንጅት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሷል ።

በውይይቱ ወቅት ግልፀኝነት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ከሰልጣኞች ጥያቄ ተነስተው ውይይት ተደርጎ ማብራሪያ ተሰጥቷል ።

በስልጠናው የክልሉ ቢሮ የዘርፉ ባለሙያዎች ከዞን፣ ከወረዳና ከከተማ አስተዳደር የመጡ የታክስ መረጃ አደራጅ፣ የታክስ ህግ ተገዥነትና የስጋት ስራ አመራር ባለሙያዎች ተሳታፊ ነበሩ።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *