የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 12ኛ አመት የስራ ዘመን11ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሚዛን አማን እያካሄደ ይገኛል።
የቤንች ሸኮ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ጌዲዮን ኮስታብ እንደገለፁት ለዞኑ ህዝብ ፈጣን ልማት፤ ዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና መልካም አስተደደር መስፈን የዞኑ ምክር ቤት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።



በየደረጃዉ ያሉ ምክር ቤቶችን አቅም በመገንባትና በመደገፍ በሶስቱ የመንግስት አካለት የህዝብን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በህገ መንግስቱ በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት አቅዶ ተግባራትን ለማከናወን ለዚሁ ምክር ቤት አቅርቦ መጽደቁ የሚታወስ መሆኑን ጠቁመዋል ።
በ2017 በጀት ዓመት የታቀዱት ተግባራት በታቀደዉ ልክ ተግባራዊ ተደርገዉ የህዝቡን ተጠቃሚነት መረጋገጡን፣ ለህዝቡ ኑሮ መሻሻል፣ ለሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የሚያግዙ ተግባራቶች መከናወናቸዉን ለማረጋገጥ በየደረጃዉ ባሉ የምክር ቤቱ አደረጃጀቶች የተደረጉ የግምገማ፣ የክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ ሥራዎች ዉጤታማና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ሲሉም ጠቁመዋል ።
የምክር ቤቶቻችን ውሳኔ የማስተላለፍና የማስፈጸም አቅም ከነ ጉድለቱም ቢሆን አበራታች መሆኑን የተከበሩ ዋና አፈጉባኤው ተናግረዋል።
በየደረጃዉ ከአስፈጻሚዉ ጋር በቅንጅት በምክርቤቱ ተወስነዉ የሚፈጸሙ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች አበራታች ዉጤት ማምጣት መቻላቸዉን በተጨባጭ በመስክ ምልከታ በተግባር ማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የታችኛዉ ምክርቤቶቻችንን የመፈጸም አቅም ወጥ የማድረግ ሥራ ቀጣይ ትኩረት የሚፈልግ ነዉ፡፡
በአጠቃላይ ምክርቤቱ በበጀት አመቱ ሊያከናዉን ያቀዳቸዉን ዋና ዋና ተግባራት በዕቅዱ መሰረት የፈጸመ ሲሆን ከጉድለቶች አንጻር የሚቀመጡ አቅጣጫዎችን ተቀብለን የምናርም ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚካሄደው ጉባኤ የህግ አዉጪዉን፣ የአስፈጻሚውንና የህግ ተርጋሚዉን የአመቱን አፈጻጸም ገምግሞ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ መሆኑን የተከበሩ አቶ ጌዲዮን ኮስታብ ጠቁመዋል ።
የ2018 ዕቅድ ማስፈፀሚያ በጀት ቀርቦ እንደሚፀድቅ እና የተለያዩ ሹመቶች ቀርበው እንደሚፀድቁ በመረሃ ግብሩ ተጠቁሟል ሲል የቤንች ሸኮ ዞን የመንግሰት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል ።
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተላሉን ![]()
በፌስቡክ https://www.facebook.com/sowestcommunication/
በድረገጽ www.southwestcomunications.gov.et
በኢንስታግራም https://instagram.com/southwest_communications
በትዊተር twitter.com/sweprs
በቲክቶክ https://www.tiktok.com/@southwest.communi
በቴሌግራም https://t.me/Debubmierab
በዩቲዩብ youtube.com/@southwestgovcommunication
በዋትስአፕ
https://whatsapp.com/channel/0029VbAiSCpGE56ue7VyJJ3x
https://www.linkedin4v .com/company/southwest-communications/
